ማስታወቂያ የቪዛ ማመልከቻ ቅጽ ሙሉ ለሙሉ ድጂታል ስለ ማድረግ እና የ ኦንላይን ቀጠሮ ስለማስያዝ
2019-01-25 16:49

ክቡራን ኣመልካቾች የቻይና ህዝብ ሪፐብሊክ ኤምባሲ በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊት ሪፓብሊክ እ.ኤ.ኣ ከየካቲት 01,2019 ጀምሮ  ኣመልካቾች ሙሉ ለሙሉ በኦንላይን የቪዛ ማመልከቻ ቅጽ የሚሞሉበትን እና ቀጠሮ የሚያሲዙበትን ኣሰራር በይፋ ይጀምራል። መሟላት ያለባቸው የሚከተሉት ይሆናሉ፡

1. በሚከተለው ድረ-ገጽ ላይ የቪዛ ማመልከቻ ቅጽ (visa application form) ኦንላይን በመሙላት የማመልከቻ ቅጹን እና የማረጋገጫ  ቅጹን(confirmation form)በማተም(print)በማድረግ የማረጋገጫ ቅጹ ላይ ይፈርሙ። https://cova.cs.mfa.gov.cn

2. ቀጠሮ ለማስያዝ የሚከተለውን ድረ-ገጽ ይጠቀሙ https://avas.cs.mfa.gov.cn

3. በቀጠሮ ቀን የቪዛ ማመልከቻ ቅጹን፣ የማረጋገጫ ቅጹን፣ ፓስፖርቱን እና ሌሎች ኣስፈላጊ ሰነዶችን ይዘው በኣካል ወደ ኤምባሲው ይምጡ።

4. በመርህ ደረጃ የበጣም ኣስቸኳይ (express urgent)ኣገልግሎት ኣይስጥም። ካለ ቀጠሮ ወደ ኤምባሲው በኣካል የሚመጡ ኣመልካቾችን ኣናስተናግድም።

             ለትብብራቹ እናመሰግናለን።

 

 

የቻይና ህዝብ ሪፐብሊክ ኤምባሲ

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊት ሪፓብሊክ

01, 22, 2019 እ.ኤ.ኣ